የግእዝ ክፍል
ስለ ግዕዝ ምንነት |
ግዕዝ ፡ በአፍሪካ ቀንድ ፡ በኢትዮጵያና ፡ በኤርትራ ፡ በጥንት ፡ የተመሠረተና ፡ ሲያገለግል ፡ የቆየ ፡ ቋንቋ ነው። የግዕዝ ፡ አመጣጥ ፡ በግምት ፡ የዛሬ ፡ ፫ ፡ ሺህ ፡ ዓመት ፡ ከየመን ፡ እና ፡ ደቡብ ፡ አረቢያ ፡ በመነሣትና ፡ ቀይ ፡ ባሕርን ፡ በመሻገር ፡ ሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ከሰፈሩ ፡ የተለያዩ ፡ የሳባውያን ፡ ነገዶች ፡ ቋንቋና ፡ በጊዜው ፡ ሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ ይነገሩ ፡ በነበሩ ፡ ቋንቋዎች ፡ ዘገምተኛ ፡ ውኅደት ፡ ነው።በአክሱም ፡ መንግሥትና ፡ በኢትዮጵያ ፡ መንግሥት ፡ መደበኛ ፡ ቋንቋ ፡ ነበር።
ግዕዝ ፡ ከአማርኛና ፡ ሌሎች ፡ ኢትዮ-ሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ ጋር ፡ ሲወዳደር ፡ «ንጹሕ» ፡ ሴማዊ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። ግዕዝ ፡ እስከ ፡ ፲ኛው ፡ ክፍለ-ዘመን ፡ መጀመሪያ ፡ ድረስ ፡ ዋነኛ ፡ የመግባቢያ ፡ ቋንቋና ፡ ልሳነ ፡ ንጉሥ ፡ ነበር።ከ ፲፫ኛው ፡ ክፍለ ፡ ዘመን ፡ ጀምሮ ፡ ግን ፡ ሙሉ ፡ በሙሉ ፡ መነገር ፡ አቁሞ ፡ በሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ በትግርኛ ፡ እንዲሁም ፡ በማዕከላዊው ፡ ክፍል ፡ ደግሞ ፡ በአማርኛ ፡ ተተካ።ዛሬ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋሕዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ሥነ-ስርዓት ፡ እንዲሁም ፡ በኤርትራ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋሕዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፣ በኢትዮጵያ ፡ ካቶሊክ ፡ ቤተክርስቲያን እና ፡ በቤተ-እስራኤል ፡ ሥነ-ስርዓቶች ፡ ይሰማል። |
የግዕዝ ፊደላት |
በግዕዝ ፡ ጽሕፈት ፡ ፳፮ ፡ ፊደላት ፡ ብቻ ፡ ይጠቀሙ ፡ ነበር ፤ እነርሱም፦
ሀ ፣ ለ ፣ ሐ ፣ መ ፣ ሠ ፣ ረ ፣ ሰ ፣ ቀ ፣ በ ፣ ተ ፣ ኀ ፣ ነ ፣ አ ፣ ከ ፣ ወ ፣ ዐ ፣ ዘ ፣ የ ፣ ደ ፣ ገ ፣ ጠ ፣ ጰ ፣ ጸ ፣ ፀ ፣ ፈ ፣ ፐ ናቸው። |
ግስ |
ግስ ማለት ቀለም አገስጋሽ ማለት ነው፤ ምክንያቱም ማንኛውም አርፍተ ነገር ያለ ግሥ የምይነገር የማይገሠግሥም ነውና፤
እርባታው ሁሉ ሲዎርድ ግሥ ወረደ ይባላል። |
የቃላት ፍች |
ነገርክሙ - ነገራችሁ
ነገራ - እነርሷ ነገሩ ይንግሩ - ይነግራሉ |
እርባታ |
አእምረ |
ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ቀ በ ተ ኀ ነ
|